መልቀቅ
Apr 28, 2021 • መጋቢ ዘካርያስ በላይ
እግዚአብሔርን በአንድ ላይ ስናመልክና ስናገለግል በመንፈሳዊ ህይወታችን ከሚያስፈልገን ነገር አንዱና ዋናው እርስ በእርስ መቀባበል ነው:: በዚህ መቀባበል ውስጥ አንዱ ለሌላው መንፈሳዊ በረከት ይሆናል:: ይህ እንዲሆን ደግሞ እይታን ማስተካከል የግድ ነው:: ይኸውም ሰውን በተላንትና ድካሙና ባልበቃበት በኩል ያለውን በመቁጠር ሳይሆን እግዚአብሔር እንደሚያይ አይቶ በመልቀቅ ነው:: ሰለዚህ ሌሎች በእኛ ህይወት ውስጥ መነፈሳዊ በረከት ሊሆኑን የሚችሉት እኛ የለቀቅናቸውን ያህል ነው:: እኛም ለሌሎች መንፈሳዊ በረከት መሆን የምንችለው እንዲሁ ሰዎች እኛን በለቀቁን መጠን ነው::
- አማኝ በውስጡ ያለው ፀጋ ጎልቶ እንዲወጣ እንዲጠቅምና ለበረከትም እንዲሆን ሊለቀቅ ያስፈልጋል::