አይኖቻችንን እባክህ ግለጥ
Apr 16, 2021 • መጋቢ ደርጀ ኃይለየሱስ
አማኝ ተስፋውን አፅንቶ እንዲይዝ ደግሞም በሰማው ህያው ቃል ላይ በእምነት መቆም ይሆንለት ዘንድ የመንፈሳዊ አይኖቹ መከፈት ዋና ነገር ነው::
መንፈሳዊ አይኖቻችን ሲያዙ:-
- ኢየሱስን ከሙታን መንደር እንፈልገዋለን:: ህያውነቱ ይሰወርብናል::
- ከሰማነው ህያው ቃል እሩቅ እንሆናለን::
- በእምነት ሳይሆን ስጋዊ አይኖቻችንና እውቀታችን በሚመሩን ብቻ እንጓዛለን::
- ከአድናቆት ያለፈ ህይወት አይኖረንም::
- ተመራማሪ እንሆናለን::
አይንን የሚከፍት እርሱ ጌታ እግዚአብሔር ነው:: ከእውነተኛው መአድ በመካፈልና በመመገብ አይን ይከፈታል:: ወደ እውቀት ወደ መረዳትም ያመጣናልና::