ኢየሱስን መከተል:: ዮሐ.21:1-22

May 5, 2021    መጋቢ አለማየሁ ሙሉጌታ

የአማኝ ህይወት በምድር ላይ ጌታን በማመን ብቻ የሚቆም ሳይሆን ነገር ግን የጌታ ተከታይ ደቀመዝሙር በመሆን የሚቀጥል ነው:: የክርስትና መንገድ ኢየሱስን እያየን የምንሄደው የመከራ ደግሞም የተስፋና የበረከት የሰላም መንገድ ነው::
ኢየሱስን መከተል:-
- በራስ ላይ መፍረድን የራስን መተው ይጠይቃል::
- አሰቀድሞ ዋጋ መተመንን ይፈልጋል::
- መጣል ያለብንን መጣል መውጣት ካለብንም መውጣት የግድ ነው::
-ባልተከፈለ ልብ ፍፁም እኛነታችንን ሙሉ በሙሉ መስጠትን ይጠይቃል::
- ጌታን ስንከተል እርሱን እያከበርንና ለእርሱ ምስክሮች በመሆንም ነው::
- መከተል እስከፍፃሜ መሄድ ነው:: በምናልፍባቸው በማንኛውም ነገርና ሁኔታ ውስጥ ፀንቶ መከተል ነው::