ለወጥመዱ አለመመቸት

Apr 21, 2021    መጋቢ ዘካርያስ በላይ

እግዚአብሔር በህይወታችን ላለው አላማ ስንኖርና ሰንጓዝ ጉዟችንን ለማሰናከል ሰይጣን ወጥመድ ማዘጋጀገቱ የማይቀር ነው:: ይህ የእርሱ የአለት ተእለት ተግባሩ ነውና:
ለወጥመዱ የምንጋለጠው ወይም ምቹ የምንሆነው :-
- ብዙ ተመክረን ወይም ተገስፀን አንመለስ በልንበት በዛ ወጥመድ አለ::
- በችኮላ ባለማስተዋል ዘለን የምንገባበት ሁኔታ ለወጥመዱ ምቹ ነው::
- ያለ ንፅህናና ያለ ቅድስና ያለ እውነትና ያለ እምነት ባልሆንበት::
- ጌታን በርቀት መከተል እንዲሁም የማይገባ ክብርና ዝና ወደ ወጥመዱ ስበው ይከቱናል::
በህይወት ጉዟችን ከክፉው ወጥመድ የምንሰወረው ወይም የምናመልጠው :-
- እግዚአብሔርን መፍራት ዋናው ከወጥመዱ ማምለጫ ነው::
- ለመንፈስ ቅዱስ ምቹ በሆንበት
- ቅድስናና ፅድቅ በመረጥን ጊዜ አንዲሁም የቃሉን እውነት ትህትናን እና አውነትን...ወዘተ በመረጥን ጊዜ ወጥመዱን እናመልጣለን::