የእግዚአብሔር ምስክር
Apr 8, 2021 • መጋቢ ሰይፈ በቀለ
የእግዚአብሔር ህዝብ የእግዚአብሔር ምስክር ነው:: ማዳኑን ታላቅነቱንና ድንቅ ስራውን የሚመሰክር:: እግዚአብሔር እስራኤልን በድንቅና በተአምራት ከባርነት ነፃ ሲያወጣ የእስራኤል አምላክ ተብሎ ታላቅ ስሙ በህዝቡ ላይ ተጠርቷል::
በዚህ አለም የመኖራችን አንዱና ዋናው ምክንያት ከጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃኑ የጠራንን የማዳኑንም ሥራ ልንናገር በቃልና በስራ ምስክር ልንሆን ነው:: ለዚህም የሚሆን የሚረዳ የሚያግዝ የእግዚአብሔር ፀጋ አለ::