ባልንጀራህ ማን ነው
Apr 5, 2021 • መጋቢ ዘካርያስ በላይ
ሰው ኃጢአተኛና ከእግዚአብሔር ክብር የጎደለ ከመሆኑ የተነሳ በራሱ መልካም መሆንና ጽድቅንም መፈፀም አይችልም:: ሰለዚህ የሆነውና እያደረግንም ያለው በጎና መልካም ነገር ሁሉ ሁኑ ካለን ደግሞም እንደፈቃዱ እንድንሆን የሚረዳንን ፀጋ ከሰጠን ከእግዚአብሔር ነው::
ጌታ የበዛውን ኃጢአትና ድካማቸንን አልፎ ነው የረዳን ነፃ ያወጣን:: አግዚአብሔር በእኛም ህይወት ይህንን ለሌሎች መሆንን መድረስን ማየት ይፈልጋል::
ከእግዚአብሔር የተቀበልነው ደግሞም ወደ ፊቱ በቀረብን ጊዜ ሁሉ የሚሰጠን ፀጋ የልጁን መልክ እንድንመስል የሚያሰችል ፀጋ ነው::