እግዚአብሔር ጣልቃ ሲገባ
May 3, 2021 • መጋቢ ዘካርያስ በላይ
በአማኝ ህይወት ውስጥየእግዚአብሔር ፅድቅ ከሚገለጥበት አነዱ ጣልቃ መግባቱ ነው:: ለማዳን ከጥፋት ለመመለስ ደግሞም የክፉውን ስራ ለማፍረስ:: በምናልፍበት የትኛውም ፈተናና መከራ በእግዚአብሔር ዘነድ ገደብ አለውና ከገደቡ እንዳያልፍ እርሱ ጣልቃ ይገባል::
- ለእግዚአብሔር በህይወታችን ጣልቃ መግባት የኛ በፅድቅ መቆምን በእውነትና በቅድስና ደግሞም በንፅህና መሆንን ይጠይቃል:: የን ጊዜ ካልተጠበቀ ስፍራና ሁኔታ የእርሱን ጠልቃ መግባት ያሳያል::
- አንዳንድ ጊዜ በህይወታችን ጌታ ጣልቃ የመግባቱ ሁኔታና አደራረጉ ላይገባን ይችላል:: ደግሞም ነገሮች አንደምንጠብቃቸው ላይሰካኩ ፍፁምም ሊፈራርሱ ይችላሉ:: እግዚአብሔር ጣለቃ ሲገባ እኛ እንደምናየው የዛሬን ወይም ለዛሬ ብቻ ሳይሆን ወደፊት ሊሆን ያለውን ከማወቁና ለእኛም ከሚጠቅመን አንፃር ነው::