ወደ ፈት መመልከት
May 5, 2021 • መጋቢ ዘካርያስ በላይ
ወደፊት መመልከት እድንችል ያለፈውን ታሪካችንን እየረሳን በተፈወሰ ማንነት ወደኋላ ማየት እስከሚያቅተን ድረስ እግዚአብሄር ነጻ ያወጣናል
ይቀይርልናል
ከኛ የሆነ መፍትሄን ለማግኘትም ብዙ ብንጥርም መፍትሄን ስለማናገኝ የእይታ ለውጥ ያስፈልገናል፤
ህይወታችን ተቀይሮ እይታችን ካልተቀየረ ፈውስ ልናገኝ አንችልም ያለፈውን እያስታወስን ለምን ሆነብኝ እያልን በባለፈው ዕይታ ነገን ለምንመለከት እግዚአብሄር ጣልቃ ይገባልንና ንጻ ያውጣናል
ስለዚህ ካለፈ ነገር ስንፈወስ ነገን በተስፋ መጠባበቅ እንችላለን
ነጋችንን ስናይ በትላንቱ እይታ ማየት ወደክስረት ስለሚወስደን የእይታ ለውጥ ማግኘት ዋና ነገር ነው