የክብር ተስፋ ያለው ክርስቶስ ከእኛ ጋር ነው
Apr 8, 2021 • መጋቢ አማረ ተክሉ
በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን ልጆች ላደረገን ለአኛ እግዚአብሔር ያወረሰን ርስት እርሱን ራሱን ነው:: ይኸውም የክብር ሙላት ያለው ጌታ ፀጋንና እውነትን ተሞልቶ በእኛ ማደሩ ነው::
አይኖቻችን ተከፍተው ያለን ርስት ክብሩና ታላቅነቱ ምን ያህል እንደሆነ ልናይ ያስፈልጋል:: ሐዋርያውም ሰለዚሁ ጉዳይ ነው እፀልይላችኃለሁ ያለው::
የክብር ተስፋ ያለው ጌታ ከእርሱ ጋር እንደሆነ አይኖቹ ተከፍተው ያየና የተረዳ አማኝ እርሱ በሚሞት ስጋ ውስጥ ቢሆንም ነገር ግን በሞት ላይ አሸናፊ ካደረገው ጌታ የተነሳ ከሞት ባሻገር ክብር በሞላበት የዘላለም መንግስት በክብር እንዲኖር ይረዳል:: ደግሞም በብዙ ችግርና ፈተና ውስጥ ቢያልፍም እንኳ ታላቅ ሰላምና ደስታን የተሞላ የእውነትም አገልጋይ ይሆናል::