ታላቅ ብድራት ያለውን ድፍረታችንን አንጣል - ክፍል 4

Apr 21, 2021    መጋቢ አለማየሁ ሙሉጌታ

እግዚአብሔር በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ሞትና ትንሳኤ ወደ መንግስቱ እንድንገባ ብቃት ሆኖናል:: ደግሞም ወደዚህ ወደ ከበረው የዘላለም መንግስት መግባታችን በሙላት እንዲሆንም የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው::
- ወደ እግዚአብሔር መንግስት የገባንና የከበረ ተስፋ ያለን አኛ ሁልጊዜ ልናስብና በተግባርም ልንኖርበት የሚገባን አራት ዋና ዋና ምክሮችን በዚህ ትምህርት በጥልቀት እንማራለን:-
1 - ከቅዱሳን ጋር ያለንን አንድነት በመጠበቅ ፀጋን መካፈል::
2 - ወደ ኃላ የሚጎትተንን ሸክምና ኃጢአት በየእለቱ በማስወገድ መሄድ::
3 - እግዚአብሔርን በመፍራትና በማክበር በፍቅር በፅደቅና በቅደስና በሰላምም መኖር::
4 - ከስህተት ትምህርት መጠበቅ:: ከተቀበልነው የከበረ ተስፋና እውነት ከሚያወጣና ከሚያዝል ከሚያደክም ትምህርት መጠበቅ:: የዳንበትንና የተመሰረትንበትን የእግዚአብሔር ቃል እውነት ጠንቅቀን ልናውቅ የከበረውንም ተስፋ አጥብቀን ልንይዝ ያስፈልግል::