መነፈሳዊ ጦርነት - ክፍል 4

Apr 14, 2021    መጋቢ ዘካርያስ በላይ

በማንኛውም ሰአትና ቦታ የምንናገረውንና የምናደርገውን ካልተጠነቀቅንና በእምነትና በፀሎት ከእውቀትና እንደ እግዚአብሔር ቃል ካልሆነ ለጠላት ፍለፃውን መወርወሪያ ምክንያት ለውጊያውም ሜዳ ያገኛል::
*** ከእኛው ወጥቶ እኛን ራሳችንን የሚዋጋበት መንፈሳዊ ጦርነት :--
-- እንደበራልን ካልተናገርን
-- በመንፈስ ቅዱስ ካልተከለልንበት
-- በመሰለን ከጌታ ቃል ያልሆነ በተናገርንበት
-- መራራነት ተሞልተን በተናገርንበት
-- ከፀሎት በፊት የፍርድ ቃል በተናገርንበት
-- ተቃራኒ ነገርን ባሰብንበት እና ልባችንን ባጠነከርንበትና ሌሎችም... በዚህ ትምህርት በጥልቀት አንማራለን::
በምንሰማውና በምናየው ነገር በመጀመሪያ በውስጣችን ብቅ የሚለው እርሱ የእኛነታችን ትክክለኛው መገለጫ ነው:: በመጀመሪያ በውሰጣችን ሊከብድ የሚገባው ምህረት ነው:: ይቅርታና ሰላም ያለበት ፍቅርና በጎነት ያለበት ነው:: ከእነዚህ ተቃራኒ ከሆነ ጠላት የሚጠቀምበት ሰለሆነ ልነጠነቀቅ ይገባል::