መነፈሳዊ ጦርነት - ክፍል 3 ሀ
Apr 13, 2021 • መጋቢ ዘካርያስ በላይ
ሰው እግዚአብሔርን በፅድቅና በቅድስና እንደ ቃሉ የሆነ ህይወት አእንዳይኖር ለማሰናከል በአምላኩም ላይ እንዲበድል ዘወትር ያለ እረፍት የሚተጋ ጠላት አለበት:: አርሱም የፅድቅ ጠላት አሳች የተባለው ሰይጣን ነው:
አማኝ ዘወትር ራሱን በጌታ ውስጥ እንደሆነ እርግጠኛ ሊሆን ይገባል:: ሰይጣን እኛን ለማሳት ለመዋጋት በርና እድል ፈንታ የሚያገኘው ራሳችንን በጌታ ውስጥ ሆነን ባልተገዛንበት በኩል ነውና:: አማኝ በእግዚአብሔር ቃል አዕምሮው ካልተቀደሰና ነፃ ካልወጣ በመንፈስ ቅዱስም ህይወቱ ካልተያዘ ለሰይጣን ፍላፃና ለስህተት አሰራሩ የተጋለጠ ይሆናል::
*** ክፉው እኛን የሚፈትንባቸውና የሚዋጋባቸው መንገዶች:-
- እግዚአብሔርን በምንበድልበት በኩል
- በምንታበይበትና በምንዳፈርበት በኩል
- በምንፈራበትና በምንሰጋበት በኩል
- ቃሉን ባዛባንበትና በእምነት ባልቆምንበት በኩል ... ወዘተ ነው:: ሰለዚህ እግዚአብሔርን በመፍራት በፀጋው ችሎት ችግራችንን ማወቅና ባወቅነው ችግርም ላይ እርምጃ ልንወስድ ይገባል::