መታዘዝ:: ክፍል 1
Apr 23, 2021
አማኝ በህይወት ጉዞው ውስጥ ፍፁም በእግዚአብሔር ሥልጣን ስር መሆኑና መገዛቱ የሚገለጠው በመታዘዝ ነው:: መታዘዝ በሌለበት ህይወት አያልፍም:: የጌታ ኢየሱስ ህይወት ወደ ሚያምኑት ሁሉ ያለፈው ከመታዘዙ የተነሳ ነው አሰከ መሰቀል ሞት የታዘዘ ሆኗል ::
እግዚአብሔር የተናገረው የበረከት ቃሎች ወደ ህይወታችን የሚያልፈው እለት እለት በታዘዝንበት በኩል ነው:: በአለመታዘዝ ምክንያት ወደ ህይወታችን ከመፍሰስ የቆመውን በረከት በፆምና በፀሎት ማግኝት አንችልም:: የእኛን መታዘዝ የሚጠይቁ ናቸውና
በአለመታዘዝ ምክንያት እስራኤል በምድረ በዳ እንደቀሩ ሁሉ እኛም በዚህ መንገድ እንዳንሄድ ህያው ቃሉ ይመክረናል::
- ለጌታ የመገዛታችን ፍሬ መታዘዛችን ነው::