መነፈሳዊ ጦርነት - ክፍል 2
Apr 12, 2021 • መጋቢ ዘካርያስ በላይ
በየትኛውም ዘመንና ጊዜ የሰይጣን ተቀዳሚ አላማ እግዚአብሔርንና የእግዚአብሔር የሆነውን መተካት ነው:: ይህን ለማድረግ ደግሞ እጅግ ረቂቅ ደግሞም የተገለጡ ዘዴዷዎችን ይጠቀማል:: ይህን አሰራሩን ደግሞ የተቀበሉ እነርሱ የክፋቱ መጠቀሚየ ይሆናሉ::
የክፋት የረኩሰትና የሀሰት ምንጭ እርሱ ነው::ሰለዚህ አማኝን ማርከስ በክፋት መሙላት አመፀኛ ማድረግ ወዘተ ... የዘወትር ተግባሩ ነው:: ወደ እግዚአብሔር ያልተጠጋ በፀሎትም ያልተከደነ ለክፋቱ የተጋለጠ ይሆናል::
*** ሰይጣን እኛን በቀጥታ ማግኘት አይችልም:: የምናመልከው ጌታ ታማኝ ነውና ከጥበቃው አልፎ ወደ እኛ የሚመጣ ሊኖር አይችልም:: ነገር ግን ወደ ስጋዊነት ባመዘንንና ከፀሎትና ከቃሉ በራቅን ጊዜ ለሰይጣነ ጥቃት የተጋለጥን እንሆናለን::
***ለአማኝ እግዚአብሔርን መፍራት ዋናው ከክፉ ሁሉ መጠበቂያው ነው::