መንፈሳዊ ጦርነት - ክፍል 1

Apr 12, 2021    መጋቢ ዘካርያስ በላይ

መነፈሳዊ ጦርነት ሰይጣን ወደ አማኝ ህይወት ኑሮና ማንነት ከሚልከውና ሊፈፅም ከሚፈልገው ክፉ ስራው ጋር መጋጠም ነው:: ሰይጣን ክፉ የሆነ ስራውን አላማውን ለመፈፀም ለማሳካት የተለያዩ መንገዶችን ይጠቀማል:: በሚያሰፈራና በሚያስጨንቅ ሁኔታ ወይም ደግሞ መልካም በሚመስል በሚሸነግል ማታለያ መንገድ ይመጣል::
*** የሰይጣን የመጀመሪያውና ዋናው ውጊያው ከህልውናችን ጋር ነው:: ለሰይጣን ትልቁ ችግር የክርስቲያን መኖር ሰለሆነ ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ አማኝን ማጥፋት ተቀዳሚ አላማው ነው::
*** አማኝ መንፈሳዊ በሆነ ጊዜ ሁሉ ጌታ እነደሚጠቀምበት ስጋዊ በሆንን ጊዜ ደግሞ ለሰይጣን ክፉ ሀሳብ መጠቀሚያ እንሆናለን:: የእግዚአብሔር ቃል እነደሚመክረን በአዕምሮአችን መታደስ ልንቀደስ ደግሞም ዘወትር መንፈሳዊ ልንሆን ዋናና አስፈላጊ ጉዳይ ነው::