መንፈሳዊ ተሀድሶ

Jun 1, 2021    መጋቢ ኪሩቤል ሃጌ

መንፈሳዊ ተሀድሶን ወደ አማኝ ህይወት የሚያመጣው እግዚአብሔር ራሱ ነው:: አላማውም የሰውን ሁለንተና ወደ ራሱ ፈቃድ መመለስ ደግሞም በቤተክርሰቲያን በአማኞች መካከል ክብሩን በመግለጥና ሰዎችን ወደ ህይወት ወደ ብርሃን ማምጣት ነው:: መንፈሳዊ ተሀድሶ ሲመጣ ምስጢር ይገለጣል:: የንስሃ ጥሪ ለሰው ሁሉ ይሆናል:: የእግዚአብሔርም የማዳኑ ጉልበት ይገለጣል:: ድንቅና ተአምራት ይሆናልም:: በዚህ መልእክት እግዚአብሔር መንፈሳዊ ተሀድሶን ወደ ህይወታችን የሚያመጣባቸውን መንገዶች እንማራለን::