የእግዚአብሔር ሐሳብ
Jan 1, 2023 • መጋቢ ዘካርያስ በላይ
መልካምን ነገር በሰው ሕይወት ውስጥ የሚጠብቅ እግዚአብሔር ነው። እኛ ፈጥነን የእግዚአብሔርን ነገር እንረሳለን። የመለኮት ሐሳብ በመንፈሱ በሃይል፣በጽኑ ክንድ ነው የሚጠበቀው። ሃያላን ይነሳሉ ይወድቃሉ። የእግዚአብሔር ሐሳብ ግን ይቀጥላል። ለምን? ምክንያቱም የእግዚአብሔር ሐሳብ ሁልጊዜ የሚጠበቀው በእግዚአብሔር በራሱ ነው።