እግዚአብሔርን የሚፈሩ

Sep 20, 2022    መጋቢ ኪሩቤል ሃጌ

እግዚአብሔርን መፍራት ትልቅ የህይወት ምእራፍ ነው ሰው እግዚአብሔርን እየፈራ ሲኖር ተግሳጽን ምክርንም ይሰማል፣ ከክፉ ይሸሻል ሰላምን ይከታተላል፣ ከአንደበቱ በሚወጣው ቃል፣ ሰውን ላለመጉዳት ይጠነቀቃል፣ እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሰዎች መገለጫቸው እግዚአብሔርን በየትም ስፍራ ማምለካቸው ሲሆን እግዚአብሔር ሊያደምጠው የሚችል ንግ ግር ደግሞ እርስ በእርስ መነጋገራቸው ነው፣ ሌላው መገለጫቸው የእግዚአብሔር ምህረት በላያቸው የገነነና ከማያምኑ ስዎች የተለዩ መሆናቸው ነው