እግዚአብሔር ሕዝቡን ያያል

Sep 4, 2022    መጋቢ ሰይፈ በቀለ

እግዚአብሔር የህዝቡን የመከራ ልክ ያውቃል፣ ሞት ህመም ስቃይ የውድቀት ውጤቶች የሀጢያት ፍሬዎች ናቸው እንኚህ ሁሉ በረደረጃው የሰውን ልጅ ሁሉ በየተራው ያገኙታል ከእግዚአብሔር ጋር የተጣበቁ ግን በእርሱ መጽናናት ያልፉታል ይህ ርህራሄን የሚያውቅ በድካማችን የሚራራልን ጌታ በሩቅ ቆሞ ሳይሆን በምናልፍበት ማንኛውም ችግር ውስጥ ከኛ ጋር ገብቶ ስሜታችንን ይካፈላል፣ ጌታችን እራሱ በስጋው ወራት ከሞት ሊያድነው ወደሚችል ወደ አባቱ ከብርቱ ጩኸትና ከእንባ ጋር ጸሎትንና ምልጃን ሲያቀርብ ፥ እግዚአብሔርንም ስለ መፍራቱ እንደ ተሰማለት እኛም በምናልፍበት የመከራ ጊዜ የሚረዳንን ጸጋ እንድናገኝ ወደ ጸጋው ዙፋኑ ሁልጊዜ በእምነት ልንቀርብ ይገባናል