እግዚአብሔር ምርኮን ይመልሳል።
Oct 26, 2022 • መጋቢ ሰይፈ በቀለ
እግዚአብሔር በዘመናት ሁሉ የማይለወጥ ኪዳኑን ጠባቂና ስለስሙ ህዝቡን የማይጥል ታማኝ አምላክ ነው።ህዝቡን ወደ ከፍታ ይመራል፣ በድል ያሻግራል፣ በረከትንም ይጨምራል። ምንም እንኳ የምናልፍበት ሁኔታ አስጨናቂና ተስፋችንን ያጨለመ ቢሆን እንኳ ጌታ ግን ከዚያም ሊያወጣን ደግሞም በበረከትና በመልካምነቱ ሊጎበኘን የታመነ ነው። ከእኛ ግን የተናገረንን ቃል በእምነት ይዞ መጠበቅ ደግሞም መታዘዝና መፅናት ይጠበቅብናል።