የእግዚአብሔር ምህረት

Dec 4, 2022    መጋቢ ሰይፈ በቀለ

የእግዚአብሔር ምህረት ማለት የተሸሸግንበት፣ የተሸፈንበትና የአምላካችን የልቡ ፍቅርና ርህራሔው ለእኛ የተገለጠበት ማለት ነው። ይህ ደግሞ የአምላካችን ባህርይ ነው። በዚህም ባህርይው በምህረቱ ባለጠጋ ነው። ሐጢአተኛውን ያዳነበትና የራሱ ገንዘቡ ያደረገበትም በዚሁ ባህርይው ነው። ስለዚህ በታላቅ ፍርሃትና መንቀጥቀጥ በፍፁም ትህትናም በምስጋና የምንኖርበት ህይወት ነው።