ከሳሻችን ተጥሏል

Jun 29, 2022    መጋቢ ደርጀ ኃይለየሱስ

ጌታ በመስቀል ላይ ዋጋ ከፍሎ ሰይጣንን አሸንፎታል ሆኖም ክርስቲያኖችን በጉልበት ማሸነፍ ስለማይችል የክርስቲያኖችን ኑሮ በመከታተል በቅናት በክስ ይመጣል፣ በእግዚአብሔር ፊት ይከሰናል በአደባባይና በሰዎች ፊት ይከሰናል የክሱ አላማ ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን ሀብረት ለማበላሸት ከዘለአለም ህይወት እንድንጎድል ለማድረግ፣ አማኞችን ለመበታተን፣ ሊያጠፋንና እኛን ከሩጫችን ለማስቆም ነው እኛ ግን ሁልጊዜ ከጎናችን ሆኖ የሚማልድልን አምላክ እንዳለን በማመን ለሰይጣን በርን ከሚከፍቱ ሐጢያትን ከመልመድና የእግዚአብሔርን ይቅር ባይነት ካለመቀበል መራዝ ይገባናል