ዉሳኔ
Jun 8, 2022 • መጋቢ ደርጀ ኃይለየሱስ
ውሳኔ አባቶችን ይመለከታል እናቶችን ወጣቶችንና ልጆችንም ይመለከታል፣ ሁላችንም በደረስንበት እንወስናለን፣ ምርጫ አለው እንጂ ማንም ሰው ከውሳኔ ነፃ አይደለም፣ የምንጠማውና የምንናፍቀው መንፈሳዊውን ነገር ከሆነ የምንወስነው ውሳኔ እንደእግዚአብሔር ሃሳብ ይሆናል ይህን አይነቱም ውሳኔ ወደ በረከት ይመራናል፣ መንፈሳዊ ረሃብ የስጋ ረሃብን ሲያመጣ መንፈሳዊ ጥጋብ ደግሞ የስጋ በረከትን ያመጣል