በፀለይንበት እንቁም
Jul 30, 2023 • መጋቢ ዘካርያስ በላይ
እውነተኛ ጸሎት ሸክምን ወይም ልመናን በእምነት ወደ እግዚአብሔር ማቅረብ ነው እውነተኛ እምነት ደግሞ እግዚአብሔርን ደጅ ያስጠናል ያለ እምነት ጸሎት ሙከራ ሲሆን በእምነት የሆነ ጸሎት ግን ስራ ነው፣ ጸሎታችንን መልሳችን ከቀደመ እምነት የለንም ስለዚህ እምነት እግዚአብሔር እንዲመልስ እንጁ እኛ እንድንመልስ አይገፋፋንም ለጸለይነው ጸሎት እራሳችን መልስ ከሰጠን እስማኤልን እናቅፋለን