እርስ በእርስ መተናነጽ

Feb 21, 2023    መጋቢ ሰመረ ወልደገብሬል

እርስ በእርስ በመተናነፅ ውስጥ ዕድገት አለ; መታነፅ በመንፈሳዊ ህይወታችን በተማርነው ቃል ስር ሰደን ማደግ ማለት ሲሆን ማደግ ደግሞ ወደፍፃሜ መሄድ ነው ይህውም እኛ እምነን የዳንንን ሁሉ በእንድነት እየተገጣጠምን በጌታ ቅዱስ ቤተ መቅደስ እንድንሆን እናድጋለን በአንድነት በእውነትና በፍቅር እንድ ላይ ነው የምናድገው በመተናነፅ እንድናድግ ነውና የተጠራነው እያንዳንዳችን እየተናነፅን ካልኖርን እያፈረስን እያላለን እንዳለን በመገንዘብ እራሳችንን ዕለት ዕለት ልንመረምር ይገባናል