እግዚአብሔር ህዝቡን ያጽናናል

Nov 27, 2022    መጋቢ ሰይፈ በቀለ

ከክፋት የሚያስመልጥ እግዚአብሔር ብቻ ነው በወደቀ አለም ውስጥ ስለአለን አንደሰው ሁሉ በተለያየ ፈተና ውስጥ እናልፋለን ግን የእኛን በመከራ ማለፍ ቀላል የሚያደርገው አለምን በአሸነፈው በክርስቶስ እየሱስ ውስጥ መሆናችን ነው፣ ሃዘን መከራና ስደት ሲደርስብን በተለያየ መከራ ውስጥ ስናልፍ ነጋችንን በሚያውቅና ከራሳችን በላይ ለኛ በሚጠነቀቅ አምላክ ደስ እያለን እናልፈዋለን ከዚህም ሁሉ በላይ ትልቁ መጽናኛችን የተባረከው ተስፋችን የክርስቶስ እየሱስ ዳግም ምጽአት ነው