የእግዚአብሔር መሆን

May 13, 2024    መጋቢ ዘካርያስ በላይ

በምድር ትልቁ ትርፋችን የክርስቶስ መሆናችን ነው ክርስቶስም የእርሱ የሆኑትን ያውቃል የጠብቃል ይታደግማል እግዚአብሔር ሁሉን ነገር የፈጠረው ለራሱ ነው ከሁሉ በለይ ደግሞ ሰውን በራሱ አምሳል በመፍጠርና የራሱ ነፃ ፈቃድ ያለው ፍጡር በማድረግ ከሌሎች ፍጥረቶች የተለየና የከበረ አደረገው ፤ፈቃድ የእግዚአብሔር የፀጋ ስጦታ ነው ። ሰዎች ነፃ ፈቃድ ስለአለን ጌታም በራሳችን ፈቃድ እንድንከተለውና የእርሱ ለመሆን መወሰናችንን ስለሚጠብቅ ይህን እግዚአብሔር የሰጠንን ይፀጋ ስጦታ ስንቀበለውና ዋጋ ስንከፍልበት የእርሱ እንሆናለን የእግዚአብሔር ሰዎች የሚያስብለን አካሄዳችን ና የአፋችን ቃል እንደእግዚአብሔር መሆኑ ነው