ሕብረታችን ከማን ጋር ነው?

Oct 31, 2023    መጋቢ ለገሠ አለሙ

ሁላችንም ወደ እግዚአብሔር ህብረት ነው የተጠራነው። ይሄ ህብረት ምናልባት አንድ ምዕራፍ በቀን መጽሐፍ ቅዱስን ከማንበብ ያለፈ ነው። ደግሞም ይሄ ህብረት አንድ ሰአት በቀን ከመጸለይ ያለፈ ነው። የዘላለም ሕይወት የምንካፈልበት ነው።