እግዚአብሔር የቅርብ አምላክ ነው። ኤር፣23-23

Aug 24, 2023    መጋቢ አማረ ተክሉ

እግዚአብሔር ከመረጠው ካዳነውና ከሚመራው ህዝብ ጋር በተገናኘ ሰለራሱ ከተናገራቸው ውስጥ አንዱ እኔ የቅርብ አምላክ ነኝ የሚለው ነው። ይህን ማመንና መረዳት ትልቅ እውቀት ደግሞም የደስታ ምክንያት ነው። ወዳጅ የምንለው እርሱ በምናልፍበት ውሰጥ አብሮን ሳይሆ በሩቅ ወይም ከውጭ ሆኖ ሊያበረታን ሊያፅናን ይሆናል። ጌታ ግን አብሮን ይሆናል። ይጋርደናል ያድነንማል።