ጥያቄ እና መልስ ክፍል 215

Mar 25, 2023    መጋቢ ዘካርያስ በላይ

የዛሬ ጥያቄዎች

1. እግዚአብሔር ወደ ራሱ ሲያመጣን የሚያለማምደን ህይወት አለ ወይ?

2. እግዚአብሔር ከእኛ ጋር እንዲሆን ምን ማድረግ ነው ያለብን?

3. አዳምንና ሄዋን ከውድቀት በኋላ ቆዳ ያለበሳቸው እግዚአብሔር ራሱን መስዋዕት አድርጎ አቅርቦ ነው ወይ?

4. በብሉይ ኪዳን ሰዎች ሀጢያት ሰርተው የሚያቀርቡትን መስዋዕት እግዚአብሔር ካልተቀበለው ነፍሳቸው ወዴት ነው የሚሄደው?

5. በብሉይ ኪዳን ካህናት መስዋዕት ሲያቀርቡ እና በዛ ሲቀሰፉ ነፍሳቸው ወዴት ነው የሚሄደው?

6. በገሃነብ እና በሲዖል መካከል ያለው ልዩነት ምንድን ነው?

7. በገነት እና በመንግሥተ ሰማያት መካከል ያለው ልዩነት ምንድን ነው?

8. መሳፍንት 11፡30- ለምንድን ነው እንዲህ ዐይነት ስለት ተሳለ? እግዚአብሔርስ ይህንን መስዋዕት ተቀብሎታል ወይ?

9. መዝሙር 116 የምንለምንበት ቀን አለ የሚለውን ሀሳብ አብራራልን።

10. ዘፍጥረት 39 በምናልፍበት ነገር እግዚአብሔር ወደ ራሱ እያቀረበን እንደሆነ እንዴት ነው የምናውቀው?

11. ሞገስ ማለት እሰውን ህትወት ላይ ተጽዕኖ ማምጣት ነው የሚልውን ሀሳብ አብራራልን።

12. ሉቃስ 18፡10-14 ከመንፈሳዊ ኩራት እንዴት ነው መውጣት የምንችለው?