በእግዚአብሔር የተሰወረ ህይወት ማንነትና ክብር
Sep 12, 2021 • መጋቢ ሰይፈ በቀለ
ኢየሱስ ክርስቶስን በማመን ከሞተ ህይወት ትንሣኤን ያገኘ ደግሞም ዳግም የተወለደ ሰው በእርሱ ውስጥ የጌታ መንፈስ አለ:: ስለዚህ ሁልጊዜ ናፍቆቱና መሻቱ ጌታን ነው:: ህይወታችን ከክርስቶስ ጋር ተሰውሯልና ከምድር በሆነው ከአመፀኝነት ከክፋትና ከትዕቢት ጋር አንተባበርም:: የትንሤኤ ልጆች ነንና በመንፈስ ቅዱስ እገዛ ከሁሉ የላቀውንና የከበረውን በላይ ያለውን ጌታ እየናፈቅን በትጋት እንኑር::