ድንገት ተገልጦ ታሪክን ለሚቀይር የክብር መገለጥ በጥማት መጠባበቅ።
Oct 12, 2022 • መጋቢ ሰይፈ በቀለ
ጌታ ኢየሱስ ወደ ህይወታችን በተለያየ ሁኔታ ይመጣል። ይጎበኘናልም። ይህ ደግሞ የአማኝ ሁሉ የዘወትር ተስፋና ጥማት ነው። አመጣጡ ግን ድንገት በመሆኑ ዘወትር በትጋት ደግሞም በፅድቅና በቅድስና ያለነቀፋ በታማኝነት ልንሆን ያስፈልጋል። የጌታን ድንገት መምጣት የሚያስተናግድ የተዘጋጀ ልብ ላላቸው ለእነርሱ ጌታ እንደ ተስፋ ቃሉ አይዘገይም ። በቶሎ ይመጣል።